Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የዱራሜ – ዳንቦያ – አንጋጫ – አመቾ መንገድ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዱራሜ – ዳንቦያ – አንጋጫ – አመቾ ዋቶ ሃላባ መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በይፋ ተጀመረ፡፡

በአስፓልት ኮንክሪት ደረጃ የሚገነባው የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

ለመንገዱ ግንባታ 1 ቢሊየን 980 ሚሊየን 658 ሺህ 256 ብር ወጪ የተመደበለት ሲሆን፥ የግንባታ ወጪው በኢትዮጵያ መንግስት ይሸፈናል፡፡

ግንባታውን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የሚያከናውነው ሲሆን፥ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርት ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ዘርፍ ደግሞ የማማከር ስራውን የሚያከናውን ይሆናል፡፡

የመንገዱ መገንባት በአካባቢው የሚመረቱ የግብርና ምርቶችን ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማድረስና የአካባቢውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡

በግንባታ ማስጀመሪያ ስነ ስርአቱ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እና የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳውን ጨምሮ የፌደራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በስላባት ማናዬ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version