አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ትልቁ እና ዘመናዊ የተባለው የእናቶች እና ህፃናት ሆስፒታል ተመረቀ፡፡
ሆስፒታሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መርቀውታል፡፡
ሆስፒታሉ በ700 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን በውስጡ ከ400 በላይ ተኝቶ መታከሚያ አልጋዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።
በ22 ሺህ ካሬ መሬት ላይ ያረፈው ሆስፒታል በተመሳሳይ ሰአት ሰባት እናቶችን በቀዶ ጥገና ማዋለድ የሚያስችል አቅም አለውም ነው የተባለው።
በተጨማሪም 100 የልህቀት ማዕከል አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ያካተተ መሆኑም ተነግሯል፡፡
በምርቃት ስነ ስርአቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ፣ የሃይማኖት አባቶች የክብር ዶክተር አበበች ጎበናን ጨምሮ የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በይስማው አደራው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

