Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ለሆኑ የኤሺያ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ለሆኑ የኤሺያ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አደረጉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከአምባሳደሮቹና ዲፕሎማቶቹ ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች፥ ቀጠናዊና በጋራ ትብብሮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

አምባሳደሩ ስለ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ፥ የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ ፥ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እና ድርድር፥ የትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ እና ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የህግ የበላይነትን ለማስከበር እና የሀገርና የህዝብን ሰላም ለማስጠበቅ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል።

በተጨማሪም ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት አምባሳደሩ።

በትግራይ ክልል በህወሓት የወደሙ መሰረተልማቶችን ጠግኖ ወደስራ የማስገባት ስራም አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ በተቃራኒ የሚነዙ የሀሰት ፕሮፓጋንዳዎች መሰረተቢስና መሬት ላይ ያለውን ሀቅ ያላገናዘቡ መሆናቸን አስረድተዋል።

ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የኤሺያ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በበኩላቸው ለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው በትግራይ ድጋፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ጋር ተባብረው ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version