አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ አስጀመረ፡፡
የአገልግሎቱ ማስጀመሪያ በደቡብ ምስራቅ ሪጅን በአዳማ ከተማ ተካሄዷል፡፡
አዳማን ጨምሮ ቢሾፍቱ፣ ዱከም፣ ገላን፣ ሞጆ እና አዋሽ መልካሳ ከተሞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
አገልግሎቱ የኢትዮ ቴሌኮም የላቀ የሞባይል ዳታ አገልግሎትን መጠቀም የሚያስችል ነው፡፡
በማስጀመሪያ ስነ ስርአቱ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

