አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች መካከል ወታደራዊ ስምምነት ተፈረመ፡፡
በደቡብ ሱዳን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ጆንሰን ጁማ ኡኮት የተመራው የደቡብ ሱዳን የመከላከያ ከፍተኛ ጀኔራል መኮንኖች ልዑክ፥ በትናንትናው ዕለት ከኢትዮጵያ አቻው ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ወታደራዊ ጉዳዮች ላይ መምከሩ ይታወቃል ፡፡
በዛሬው ዕለት ደግሞ በመከሩባቸው ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደርሰው የፊርማ ስነ ስርዓት አከናውነዋል ፡፡
ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት የወታደራዊ ደህንነቶች መረጃ ልውውጥ፣ ድንበር ላይ የሚደረጉ ህገ-ወጥ የሰዎች እና የጦር መሳሪያ ዝውውር በጋራ መግታት፣ ወታደራዊ ዲፕሎማሲን ለማጠናከር ፣ በተለያዩ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ፣ በትምህርት እና ስልጠናዎች በጋራ መስራትን ያካተተ መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

