Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ገበታ ለሀገር እውን እንዲሆን አስተዋጽዖ ያበረከቱ አካላትን አመሰገኑ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገበታ ለሀገር እውን እንዲሆን አስተዋጽዖ ያበረከቱ አካላትን አመሰገኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “የበኩላችሁን ላዋጣችሁ በሀገር ውስጥ እንዲሁም ከሀገር ውጪ የምትገኙ መላው ኢትዮጵያውያን ጥልቅ ምሥጋናዬን አቀርባለሁ።” ሲሉ አመስግነዋል።

በገበታ ለሀገር 3 ቢሊየን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ ስራው መጀመሩንም ገልጸዋል።

በአበርክቶው ግን ኮይሻ፣ ወንጪን እና ጎርጎራን ለማልማት 4.2 ቢሊየን ብር እንዲሰበሰብ ተደርጓል ነው ያሉት።

“በህብር ወዳሰብነው እንደርሳለን።” ሲሉም አክለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version