አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተመድ ሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡
46ኛው የተመድ ሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ዛሬ በበይነ መረብ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እየተሳተፉ ነው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከነገ በስቲያ ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ ከሰብአዊ መብቶች አንጻር እተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የተመድ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባችሌት ለማህበራዊ ጥበቃ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የፕረስ ነጻነት እንዲከበር እና ማህበረሰቡ በውሳኔ ሰጪነት ተሳትፎው እንዲያድግ ጠንካራ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ስብሰባው በቆይታው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የውሳኔ ሃሳቦችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!