Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቦርዱ ሁለተኛውን ዙር የዕጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ አራዘመ

አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሁለተኛው ዙር የዕጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባን ሂደትን አስመልክቶ በተለያየ ወቅት የተለያዩ መረጃዎችን ሲያደርስ እንደነበር ይታወቃል። በተጨማሪም የእጩዎች ምዝገባን አስመልክቶ ሶስት የተለያዩ ምክክሮችን ከፓርቲዎች ጋር አከናውኗል::

በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር እጩዎች ምዝገባ የተጀመረባቸው ክልልሎች/የከተማ መስተዳድሮች ማለትም
– በአዲስ አበባ
– በድሬዳዋ
– በኦሮሚያ
– በሃረሪ
– በጋምቤላ
– በቤኒሻንጉል ጉሙዝ
የእጩዎች ምዝገባ በትላንትናው እለት ተጠናቋል።

የእጩዎች ምዝገባን ዘግይተው በጀመሩ ክልልሎች እና ቦታዎች ማለትም
– በአማራ
– በሶማሌ
– በአፋር
– በምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞን ኦሮሚያ፣
– በደ/ብ/ብ/ህ
– በሲዳማ
በመርሃ ግብሩ መሰረት ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ሊጠናቀቅ እንደሚገባው ይታወቃል።

ነገር ግን በቢሮዎች መከፈት መዘግየት የተነሳ፣ እንዲሁም የትራንስፓርት እና ሌሎች እክሎችን እና የፓርቲዎች አቤቱታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁለተኛ ዙር የእጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን እያሳወቅን ፓርቲዎች በተሰጡት ተጨማሪ ቀናት ውስጥ ምዝገባቸውን አንዲያጠናቅቁ እናሳስባለን፡።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version