Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቦርዱ 47 ፓርቲዎችንና 8 ሺህ 209 እጩዎችን መመዝገቡን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 47 ፓርቲዎችንና 8 ሺህ 209 እጩዎችን መመዝገቡን አስታወቀ፡፡

ቦርዱ በ673 የምርጫ ክልሎች ላይ ነው የእጩዎች ምዝገባ ያካሄደው፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ለ22 ቀናት በተካሄደው የእጩዎች ምዝገባ በምርጫው 125 ግለሰቦች በግል ለመወዳደር በእጩነት መመዝገባቸውም ተገልጿል፡፡

አራት ፓርቲዎች ለክልል ምክር ቤት ብቻ የተወዳደሩ ሲሆን ሁለት ፓርቲዎች ደግሞ ለተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ ናቸው ብለዋል፡፡

ቦርዱ በሂደቱ ወቅት ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮችም ተዳሰዋል፡፡

ከነዚህም መካከል የቁሳቁስ ማጓጓዣ ለማጓጓዝ የትራንስፖርት ትብብር ማነስ፣ የቁሳቁስ ማዘጋጃ ቦታና ቢሮ ባለመሟላት የተፈጠሩ መዘግየቶችና የሰላምና ፀጥታ ያጋጠሙ ችግሮች  መሆናቸውም ተጠቅሰዋል፡፡

ችግሩንም ለመፍታት ተከታታይ ውይይቶችን የኦፕሬሽን ዘርፍ በማቋቋም ለመፍታት ጥረት ማደረጉም ነው ሰብሳቢዋ ያስረዱት፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version