አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ ሲያትል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የኢትዮጵያን ስም ለማጠልሸት የጁንታው ርዥራዦች በክፍያ የሚሰሩትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ የሚያወግዝ ሰልፍ አካሂደዋል።
በውጭ ያሉ የጁንታው ቡድን አባላት ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ከኢትዮጵያ ህዝብ በዘረፉት ገንዘብ የሎቢ ቡድኖችን በመቅጠር ፣ ደጋፊዎቻቸውንና ግብረአባሮቻቸው በማስተባበር የኢትዮጵያን ስም ለማጠልሸት እና የዲፕሎማሲ ጫና ለመፍጠር እየሰሩ እንደሚገኙ ሰልፈኞቹ ገልጸዋል።
በዚህም ሁለቱ የአሜሪካ ምክር ቤቶች የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በጥሞና እንዲመለከቱት ሰልፈኞቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሰልፈኞቹ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የጁንታው ቡድን የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ላይ የፈጸመውን የሀገር ክህደት ወንጀልንም አውግዘዋል።
ከዚያም ባለፈ አሁን በተከፋይ የጁንታው ቡድን የሀገሪቱን ሉዓላዊነት በሚያስከብረው እና ከ20 ዓመታት በላይ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ የሕዝቡን ደህንነት ሲጠብቅ በኖረው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የተከፈተውን የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አጥብቀው እንደሚያወግዙ ሰልፈኞቹ ገልጸዋል።
ሰልፈኞቹ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ እየተካሄደ ያለውን የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲገነዘበው ለማድረግ 12 ገጽ የአቋም መግለጫ ለሚመለከታቸው አካላት ማስገባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጥህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

