Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ክልላችን እና ሀገራችን ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ የለውጡን የሽግግር ምዕራፍ በአስተማማኝ ሁኔታ መሬት ለማስያዝ እየሰራ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጅ ከለውጡ ተቃራኒ የቆሙ ሀይሎች በሙሉ አቅማቸው ለጥፋት እና ለአፍራሽ ተግባር እያዋሉት ይገኛሉ፡፡

ከለውጡ ተቃራኒ በጥፋት ስራ ላይ ተሰማርተው ሌት ከቀን ከሚሰሩት መካከል የህወሓት ተላላኪ የሆነው ኦነግ ሸኔ አንዱ ነው፡፡

ይህ ሀይል የመንግስት መዋቅር በሀይል ለመናድ የጥፋት ሰንሰለት እና እልቂት በየደረጃው ለማደራጀት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

የጁንታውን ተልዕኮ በመቀበል በመስራት ያለው ይህ ሀይል በገጠር እና በከተማ ባለስልጣናት እና ዜጎችን የሚገድል ቡድን በማሰማራት በርካታ የሽብር ጥቃቶችን አድርሷል፡፡

ከዚህ ባለፈም በርካታ የመንግስት እና የዜጎችን ንብረት አውድማል፡፡

መንግስት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በወሰደው እርምጃ የኦነግ ሸኔ ሀይል ቢዳከምም፥ በተስፋ መቁረጥ ስሜት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚወስደው የሽብር ጥቃት አሁንም ቀጥሏል፡፡

በትናንትናው እለት በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ ቦኔ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሽብር ጥቃት በመፈጸም ለግዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ተገድለዋል፡፡

በዜጎች ህይወት ላይ በደረሰው ግድያ እና በዚህ የጭካኔ እና አሰቃቂ ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች የክልሉ መንግስት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡

እንደ ክልሉ መንግስት ይህ ድርጊት በተፈጸመበት ስፍራ አፋጣኝ ክትትል እና የሽብር ጥቃቱን በፈጸመው አካል በተወሰደው እርምጃ የተወሰኑትን መደምሰስ ተችሏል፡፡

ይህ ሀይል የብተና እና የመጨራረስ ምኞት ያለው እና ከሀገር ግንባታ በተቃራኒው የሚቆም በመሆኑ ህዝባችን በሁሉም ቦታ ተደራጅቶ የጥፋት እቅዱ እንዲመክትም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የክልሉ በተከታታይ የሚወሰዱ እርምጃዎችን እንደሚገልጽም የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት

አዲስ አበባ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version