አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁሉም ነገር መሰረትና የችግሮች ሁሉ መፍትሔ ሰላምና ሰላም ብቻ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናገሩ፡፡
ዓመታዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የጉባኤውን መከፈት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የሁሉም ነገር መሰረትና የችግሮች ሁሉ መፍትሔ ሰላምና ሰላም ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ስለሆነም መንግስትም ሆነ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ አስፈላጊው ነገር ሀሉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል፡፡
ዋስትና ያለው ሰላም በሀገሪቱ ሊረጋገጥ የሚችለው ሀሉም ባለ ድርሻ አካላት በጠረጴዛ ዙሪያ ተሰብስበው መወያየት ፣ መግባባትና ሀገራዊ ስምምነት መድረስ ሲችሉ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በሀገሪቷ በተለያዩ አካባቢዎች በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ጉባኤው በጸሎት፣ በማስታረቅ፣ በቁሳቁስና በመጠለያ እንዲሁም በምግብና መጠጥ ድጋፍ ከጎናቸው ሊቆም ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በቅዱስ ሲኖዶሱ ዓመታዊ ምልዓተ ጉበኤ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርሰቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ሁሉም የአሁግረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
በመላኩ ገድፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!