አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋራ ስንተባበር ኢትዮጵያን ከፍ ማድረግ እንደሚቻል ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።
የኦሮሚያ ልማት ማህበር አመታዊ ኮንፈረንስ በአንድነት ፓርክ እየተካሄደ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው “ይህን ቀን የደረስነው እንደ ሀገር ትልቅ ዋጋ ከፍለን ነው” ብለዋል፡፡
“ያገኘነውን ድል በጋራ መንከባከብ አለብን” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አሁን በውጭም በውስጥም የተደቀኑብንን ችግሮች አንድ ከሆንን ለማለፍ የሚከለክለን የለም” ብለዋል በንግግራቸው።
በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አክኒውሚ አዲሲና በበኩላቸው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣታቸው ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ባንኩ እስከ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በሚደርስ ወጪ በኢትዮጵያ እያደረጋቸው የሚገኙትን የተለያዩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ባንኩ በኢትዮጵያ በግብርና ትራንስፎርሜሽን በሀይል ትራንስፖርት ንፅህና እና በሌሎች ዘርፎች አጋር በመሆን እየሠራ ይገኛል።
በአፈወርቅ አለሙ እና በትዝታ ደሳለኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

