Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሰራዊቱ ለህግና ለሞራል የሚገዛ በመሆኑ በህዝብ ላይ ከመተኮስ መስዋትነትን መርጧል-የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በህውሃት የሽብር ቡድን ላይ ህግን ለማስከበር የተሰጠውን ግዳጅ በሚገባ የተወጣ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ÷ መከላከያ ሰራዊት በተካሄደው ዘመቻ በሽብር ቡድኑ ንጹሃንን ሽፋን በማድረግ በተከፈተበት ጥቃት ብዙ መስዋትነት መክፈሉን አውስቷል፡፡

ይህም ለህዝብ ባለው ውግንና ሲል ሰራዊቱ ለሃገር የከፈለው መስዋትነት መሆኑን ነው ያብራራው፡፡

የሽብር ቡድኑ እንደለመደው የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን በተለያየ መንገድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ስም ለማጥፋት ቢሞክርም ሰራዊቱ ለህግ ለሞራል የሚገዛ በመሆኑ በህዝብ ላይ ከመተኮስ መስዋትነትን መርጧል ነው ያለው፡፡

የሽብር ቡድኑ ሰራዊቱ ለህዝብ የከፈለውን መስዋትነት እንደሽንፈት ቆጥሮ ለፕሮፓጋንዳ ቢያውለውም የመቀሌና የትግራይ ህዝብ የሰራዊቱን ጨዋነት እና ከአካባቢው የወጣበት መንገድ ያውቃልና በዚህ የማይታለል መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያን ህዝብ ደጀን ያደረገ ሰራዊት ሁሌም አሸናፊ እንደሚሆን መገለጹንም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version