አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባውን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ነው እያካሄደ የሚገኘው፡፡
ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው የፌዴራል መንግስትን የ2014 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚካሄደው በዚህ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

