Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 212 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 212 ዜጎች ወደ አገራቸው  ተመልሰዋል።

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎች  ወደ አገራቸው በስፋት ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎቻችን በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።

በትናንትናው ዕለትም 381 ሴቶችና 183  ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 212 ዜጎች ወደ አገራቸው ገብተዋል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል  እንደተደረገላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version