ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 212 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ከሳዑዲ አረቢያ 2 ሺህ 212 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎች ወደ አገራቸው በስፋት ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎቻችን በየቀኑ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።
በትናንትናው ዕለትም 381 ሴቶችና 183 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 212 ዜጎች ወደ አገራቸው ገብተዋል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል እንደተደረገላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!