አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዳሴውን ግድብ ድርድር ወደ አፍሪክ ህብረት እንዲመለስ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ላደረጉት አስተዋጽኦ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ምስጋና አቀረቡ።
የምክር ቤቱ አባላት ኢትዮጵያ የጀመረችው ጉዳት የማያስከትለውን የልማት ፕሮጄክት በቅንነት ስለተረዱና ድርድሩ ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለስ ስላደረጉ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አመስግነዋል።
ኢትዮጵያ የጀመረችውን ፍትሀዊ እና ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሶስትዮሽ ድርድር ፍጻሜ እንዲያገኝ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
“ባለፈው ሐሙስ ሀገሬን ወክዬ በጸጥታው ምክር ቤት ውጤታማ ገለጻ አድርጌያለሁ” ያሉት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፥ የህዳሴው ግድብ ድርድር በአፍሪካ ህብረት መፍትሄ እንደሚያገኝ እምነታቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

