አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሞሳ ፋቂ መሃማት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ሊቀ መንበሩ የቦርዱ የምርጫ ውጤት ይፋ በመደረጉ ድጋፉን የገለጹ ሲሆን፥ በምርጫው የተሳተፉ አካላትን ማመስገናቸውን ከህብረቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታሉ፡፡
የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ቦርዱ ይፋ ያደረገውን የምርጫ ውጤት ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የቁሳቁስ አቅርቦት እጥረት ፣ የኮቪድ 19 ሁኔታን ተቋቁሞ የተሳካ ምርጫ ለማድረግ በምርጫው የተሳተፉ አካላት ድርሻ የጎላ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ የሚመራው የህብረቱ ታዛቢ ቡድን በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ጳጉሜን 2 የሚካሄደውን ምርጫ የሚታዘብ መሆኑን ሊቀመንበሩ ገልፀዋል፡፡
በተያያዘም የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ በኢትዮጵያ በምርጫው ለተገኘው ድል የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንት ቡሃሪ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው ፓርቲ በምርጫው አብላጫ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር በማግኘቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን በናይጄሪያ ህዝብ ስም አድርሰዋል።
በመልዕክታቸውም “በምትከተሉት ጥሩ ፖሊሲ አማካኝነት የህዝባችሁን ኑሮ ለመለወጥ መስራታችሁን መቀጠል አለባችሁ” ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

