አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እድሪስለኢድ አል አረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአረፋ በዓል በሙስሊሙ ህብረተሰብ ዘንድ ትልቁ በዓል መሆኑን የጠቀሱት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እድሪስ፥ በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ ዱአ በማድረግ እና በአንድነት መሆን ይገባል ብለዋል፡፡
በዓሉ የሚቀጥለው ማክሰኞ የሚከበር ሲሆን፥ የሙስሊሙ ህበረተሰብ የዕምነቱን ስርዓት ተከትሎ እንዲያከብሩም ነው ሃጂ ኡመር እድሪስ ጥሪ ያስተላለፉት፡፡
ሃጂ ሙፍቲ እድሪስ በዓሉን አስመልክተው በሰጡት መግለጫም 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በሰላም በመጠናቀቁ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
ሰላም የሃገር መሰረት መሆኑን አውቀን ሰላማችንን መጠበቅ ይገባናል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ የሃገር ሰለም ለመጠበቅ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተገቢውን ድርሻ እንዲወጡ በሙስሊሙ ህበረተሰብ ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሽቦ ኂርጶ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!