አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሶማሌ ክልል ምክር 5ኛ አመት 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ በጅግጅጋ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
የ12ኛውን መደበኛ ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፣ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪፖርት ማድመጥ፣ የክልሉን ኦዲት ሪፖርት ማድመጥ፣ በ2013 ዓ.ም የክልሉን መንግሥት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ማድመጥና ማፅደቅ እንዲሁም የ2014 ዓ.ም የክልሉን በጀት ማፅደቅ የሚሉት ደግሞ በጉባዔው ለአጀንዳነት የቀረቡ ጉዳዮች ናቸው፡፡
በተጨማሪም የመንግሥት ባለስልጣናት የሀብት ማስመዝገብ የወጣ ህገ ረቂቅ ደንብ፣ የክልሉን ኦዲት ቢሮ እንደ አዲስ ለማደራጀት የወጣውን ረቂቅ ደንብ፣ የስራ ፈጠራ ረቂቅ ደንብ፣ በክልሉ የደረሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚያጣራ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ የወጣውን ረቂቅ ደንብ፣ በክልሉ ፍርድ ቤቶች የወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ምክር ቤቱ ውይይት ካደረገ በኋላ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበው የሶማሌ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

