አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል እና የክልል መንግስታት የሚሰጧቸው መግለጫዎች ሁሉ የሚያመለክቱት የኢትዮጵያ ማህበራዊ ውቅር አንድ አካል የሆነውን የትግራይ ህዝብ ሳይሆን፣ ወንጀለኛውን ህወሃትን ብቻ መሆኑን የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ ÷ የህወሓት ፕሮፓጋንዳ አራማጆች እና አጋሮቻቸው የፌደራል እና የክልል አመራሮች የሚናገሩትን በመጠምዘዝ ለብዙ ወራት ሲሸርቡ ከቆዩት የሐሰት ዜናዎች እና አጀንዳዎቻቸው ጋር ለማጣጣም መሞከራቸውን እንደቀጠሉ አብራርቷል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሃት አሸባሪ ድርጅት እንደ ሆነ ማወጁን በማገናዘብ፣ የፌደራል እና የክልል መንግስት የሚሰጧቸው መግለጫዎች ሁሉ የሚያመለክቱት የኢትዮጵያ ማህበራዊ ውቅር አንድ አካል የሆነውን የትግራይ ህዝብ ሳይሆን፣ ወንጀለኛውን ህወሓትን ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

