Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አለም አቀፍ ድርጅቶች ህወሃት ሰብዓዊ እርዳታ ለያዙ ተሽከርካሪዎች መንገዱን እንዲከፍት ግፊት ማሳደር አለባቸው – ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አለም አቀፍ ድርጅቶች ህወሃት የአፋርን ክልል መተናኮሱን አቁሞ ሰብዓዊ እርዳታ ለያዙ ተሽከርካሪዎች መንገዱን እንዲከፍት ግፊት ማሳደር እንዳለባቸው ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡

መንግስት የሰብአዊ ዕርዳታ እንዲርደስ ለማስቻል አልሞ ያደረገው የተናጠል የተኩስ አቁም በሕወሃት ትንኮሳ መደናቀፉን ቀጥሏል።

መንግስት በትግራይ ክልል በሚገኙ መጋዘኖች ውስጥ ከ400ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ስንዴ እና ከ2ነጥብ5 ሚሊየን ሊትር የሚበልጥ የምግብ ዘይት ማስቀመጡን ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል ያሉት ዜጎች ደህንነት የኢትዮጵያን መንግሥት ያሳስበዋልም ነው ያለው።

በዚህም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በተለይም ደግሞ በትግራይ ድጋፍ በመስጠት ላይ የሚገኙት፣ ህወሓት የአፋርን ክልል መተናኮሱን አቁሞ ሰብዓዊ እርዳታ ለያዙ ተሽከርካሪዎች መንገዱን እንዲከፍት ግፊት ማሳደር እንዳለባቸው አንስቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version