Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና በስዊዘርላንድ መካከል ተደራራቢ ግብርን ለማስወገድ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የስዊዘርላንድ አምባሳደር ታማራ ሞና ተፈራርመውታል፡፡
ስምምነቱ የስዊዘርላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ሀብታቸውን በልማት ስራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታትና የኢትዮጵያም ባለሀብቶች በስዊዘርላድ ገበያ ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ተደራራቢ ግብር ለውጭ ኢንቨስትመንት ማነቆ በመሆኑ ከስዊዘርላንድ መንግስት ጋር ሶስት ዙር ድርድር በማድረግ የተደራራቢ ግብርን ለማስገድ መግባት ላይ መደረሱም ነው የተገለጸው፡፡
ከፊርማ ስነ ስርአቱ በኋላ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ መምከራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version