አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 6ኛ አመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛና ማጠቃለያ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል።
በጉባኤው የክልሉ መንግስት የ2014 በጀት ዓመት የስራ እቅድ ይቀርባል እንዲሁም የክልሉ መንግስት የ2014 በጀት በክልሉ ምክርቤት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የክልሉ ምክር ቤት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፤የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2013 አፈጻጸምና የ2014 በጀት አመት እቅድም የሚቀርብ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም ልዩ ልዩ አዋጆች ይፀድቃሉ እንዲሁም ለዳኞች ሹመት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

