አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት የሽብር ቡድን ታጣቂዎች ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች እየተደመሰሱ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትአስታውቋል፡፡
የኮሙዩኒኬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ÷ የህወሓት የሽብር ቡድን ታጣቂዎች በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን በሃይል መውረራቸው ተናግረዋል፡፡
ሰርገው በገቡባቸው ቦታዎች ግድያ፣ ዘረፋ እና አስገድዶ መድፈር እየፈፀሙ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
አሁን ላይ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች እየተደመሰሱ መሆኑን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡
የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ሰርገው ከገቡበት አካባቢዎች ጠራርጎ ለማስወጣትና ለመደምሰስ ሁሉም የፀጥታ ሃይሎች በቂ የሥነ-ልቦና እና አካላዊ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
የህወሓት የሽብር ቡድን ይህንን ቦታ ያዝን ያንን ቦታ ተቆጣጠርን እያለ በሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ ትክክለኛ መረጃን ከመንግስት አካላት ማግኘት እንዳለበት ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ህብረተሰቡ በተለይ ወጣቱ አካባቢውን በንቃት እና በትጋት በመከታተል እና በመደራጀት ለሰላሙ ዘብ ሊቆም ይገባል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

