አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዩኒሴፍ ባሳለፍነው ሃሙስ በአፋር ክልል በጤና ጣቢያ እና በትምህርት ቤት ተጠልለው በነበሩ 100 ህጻናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ዜጎች ላይ የደረሰው ጭፍጨፋ እንዳሳሰበው አስታውቋል፡፡
ከሰው ህይወት መጥፋት በተጨማሪም ለተፈናቀሉ ዜጎች ሊውል የነበረ የምግብ አቅርቦት መውደሙን ነው ድርጅቱ የገለጸው፡፡
በተፈጠረው ግጭት በርካቶች እየተፈናቀሉ መሆኑን የገለጸው ዩኒሴፍ÷የሰብአዊ የተኩስ አቁሙም ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በሌላ በኩል የህወሓት አሸባሪ ቡድን በአፋር ክልል በፈጸመው ጥቃት 107 ሕጻናትን ጨምሮ 240 ንጹሃን ዜጎችን መግደሉን አልጀዚራ አጋልጧል፡፡
መንግሥት ምንም እንኳን የተናጠል የተኩስ አቁም ቢያደርግም አሸባሪው ሕወሓት በአጎራባች ክልል የሚያደርገውን ጥቃት ቀጥሎበታል ነው ያለው፡፡
ዩኒሴፍ ሁሉም አካላት ህጻናትን ከምንም በላይ እና አቅማቸው በፈቀደ ሁሉ ከጉዳት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

