አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በአሸባሪው የህዋሓት ቡድን ጥቃት የደረሰባቸው 48 ንጹሀን ዜጎች በዱብቲ አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ እንደሚገኙ የፋና የጋዜጠኞች ቡድን ከስፍራው ዘግቧል፡፡
ንጹሀን ዜጎቹ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት አስተናግደው መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ኑሩ ሰይድ ለባልደረቦቻችን ተናግረዋል፡፡
ወደ ሆስፒታሉ ለህክምና ከመጡት ንጹሀን ዜጎች መካከል አራቱ ከባድ ጉዳት ስለደረሰባቸው ወደ አዲስ አበባ ለከፍተኛ ህክምና ተልከዋል ነው ያሉት፡፡
ሽብርተኛው ቡድን በአፋር ህዝብ ላይ የፈጸመው ጥቃት የቡድኑን ከመጠን ያለፈ ራስ ወዳድነት እና ሴረኛነት ያሳዬ እንደሆነ ተጎጂዎቹ ተናግረዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ በሴቶች ህጻናት እና ሌሎች ንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸመው አሳፋሪ የፀብ አጫሪነት ተግባር የቡድኑን አረመኒያዊ ባህሪ ገሃድ ያወጣ ሰለመሆኑም ጣቢያችን ያነጋገራቸው እና በአፋር ዱብቲ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እያደረጉ የሚገኙ ተጎጅዎች አብራርተዋል።
ከአፋር ብዙሃን መገናኛ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በዱብቲ ሆሲፒታል ህክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ንጽሀን አርብቶ አደሮች እንደገለጹት÷ ጁንታው በለሊት በተኛንበት በህጻናት፣ በሴቶች እና በአዛውንቶች ላይ አሳፋሪና ዘግናኝ ጭፍጨፋ ፈጽሞብናል ብለዋል ፡፡
የተደረገብን ጭፍጨፋ በአፋር ታሪክ ውሰጥ መቼም ቢሆን የማይረሳ አሳፋሪ እና ክፉ ተግባር ነው ያሉ ሲሆን÷ ሆኖም ጁንታው መቼም እና በምንም ሁኔታ ቢሆን ወራሪነቱ አይሳካለትም ነው ያሉት ፡፡
የአፋር ህዝብ ከውጭም ከውስጥም ኢትዮጵያን ለመውረር ሙከራ ያደረጉትን አሳፍሮ የመለሰ ጀግና ህዝብ መሆኑን ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ያሉ ንጽሀን አርብቶ አደሮቹ ገልጸዋል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

