Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጁንታው የጥፋት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቀበር ተባብረን እንስራ-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የጁንታው የጥፋት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቀበር ተባብረን እንስራ ሲሉ ተናገሩ፡፡

በዛሬው ዕለት የቀድሞ የሰራዊት አባላት የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ አሸባሪው ህወኃትን የሚያወግዝ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ አካሂደዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የተገኙት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የቀድሞ የሰራዊት አባላት ለኢትዮጵያ ዘብ ለመቆም ላሰዩት ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ያሳዩት ቁርጠኝነና ተነሳሽነትም የህወሓት አሸባሪ ቡድን የሰራዊት አባላትን የአንድ የፖለቲካ ስርዓት አገልጋይ አድርጎ ሲፈርጅ መቆየቱ ምን ያክል ከእውነት የራቀ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል፡፡

የጁንታው የጥፋት ቡድን የትግራይ ህዝብንም ነው የበደለው፣ህዝቡን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ለመነጠልም ብዙ ሰርቷል ብለዋን በንግግራቸው፡፡

በዚህም ይህ አሸባሪ የጥፋት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደቀበር ተባብረን እንስራ ስል መልዕክቴን የማስተላልፈው ለትግራይ ህዝብም ጭምር ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ እበለፅጋለሁ ፣የህዳሴውን ግድብ ገንብቼ አጠናቅቃለሁ፣ህዝቦቼ እየለመኑ መኖር የለባቸውም ብላ እየሰራች ባለችበት ወቅት የኢትዮጵያን ተፈጥሮአዊ ሃብት መበዝበዝ የለመዱ፣ጫና ለመፍጠር የሚሞክሩና የኢትዮጵያን ትንሳዔ ለማደናቀፍ የሚሰሩ ሃይሎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

ሆኖም ኢትዮጵያን ከትንሳዔና ብልፅግና የሚያስቆም አንዳች ምድራዊ ሃይል የለም ሲሉ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version