አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡሔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችቶችን መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የቡሔ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚተኮሱ ርችቶችን ሽፋን በማድረግ ሰላምን የማደፍረስ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ የገዙትን የጦር መሣሪያ እንደሚፈትሹና የተለያዩ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ሁኔታዎች እንደሚፈጥሩ ፖሊስ በተለያየ ጊዜ ባደረጋቸው ጥናቶችና በደረሰው መረጃ መረጋገጡ ተጠቁሟል፡፡
በዚህም ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኝ ርችቶችን መተኮስ እንደማይችል ተገንዝቦ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
ሁኔታው ለህገ ወጦች ምቹ ሁኔታ ፈጥሮ የከተማችን የፀጥታ ስጋት እንዳይሆን ህብረተሰቡ አካባቢውን በመጠበቅ ለፖሊስ አባላት መረጃዎችን እንዲሰጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ከሚመለከተው አካል ተገቢውን ፍቃድ ሣይሰጥበት ርችቶችን በሚተኩሱ ግለሠቦችም ሆኑ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

