Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኦንላይን አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በኦንላይን በመታገዝ መስጠት መጀመሩን ዛሬ አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እና ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚሰጣቸውን የቪዛ አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን በኦንላይን መስጠት መጀመሩን ሚኒስትር ዲኤታዋ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገልጸዋል።
ይህ ይፋ የተደረገው የኦንላይን አገልግሎት መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የውጭ ሀገራት ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ድርጅቶች እንዲሁም በድርጅቶቹ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ቀልጣፋ እና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል፡፡
የአገልግሎቱ መጀመር ሚኒስቴሩ የሚሰጠውን አገልግሎት በቅልጥፍና እና በጥራት ለመስጠት የሚያደርገው ጥረት አንድ አካል መሆኑም ነው የተገለፀው፡፡
የኦንላይን አገልግሎት መስጫ ቴክኖሎጂው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ትብብር የበለጸገ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version