አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 53 ነጥብ 9 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ለስርጭት ዝግጁ መደረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።
ለዚህም 53 ነጥብ 9 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ለስርጭት ዝግጁ መደረጉን ጠቅሶ፥ ከዚህ ውስጥ 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ከበአል በኋላ የሚደርስ ነው ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም 2 ሚሊየን ኩንታል የስኳር ምርት ግዥ ተፈጽሞ ወደ ሃገር ውስጥ በመጓጓዝ ላይ መሆኑን አስታውቋል።
እንዲሁም ከመስከረም ወር ጀምሮ ወደ ሃገር ውስጥ የሚገባ 4 ሚሊየን ኩንታል የዳቦ ስንዴ ግዥ ተፈጽሟልም ነው ያለው።
በመግለጫውም የንግዱ ማህበረሰብ የኢኮኖሚ አሻጥር ላይ የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የስኳር፣ ዘይት፣ ስንዴና ሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦችን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
በህገወጥ የንግድ አሻጥረኞች ላይም እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
በዚህ ሰዓት ትርፍ ለማግበስበስ የሚደረግበት ወቅት እንዳልሆነም ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል።
ኢኮኖሚን ለማዳከም የሚደረግ የኢኮኖሚ አሻጥርን ለመግታት መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም ነው የገለጸው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

