Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ በየትኛውም ሁኔታ የማይለወጡ እንደ ደቡብ ሱዳን አይነት ወዳጆች ያስፈልጓታል – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ወቅት በየትኛውም ሁኔታ የማይለወጡ እንደ ደቡብ ሱዳን አይነት ወዳጆች እንደሚያስፈጓት ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ የትብብር ግንኙነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኑታቸውን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል። በውይይታቸው የሀለቱን ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።
ከዚህ ባለፈም በመሰረተ ልማት ግንባታ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን መገንባት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተው መክረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version