Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፖሊስ ኮሚሽን እና የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደሬራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡
በውይይቱ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የማዕድን ዘርፍ የኢኮኖሚው ዋልታ እንዲሆን እና ከማዕድን ዘርፍ እየተገኘ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ለማጠናከር በማምረት ሂደት ላይ ያሉ ክፍቶችን ለማረም ከፌደራል ፖሊስ ጋር በጋራ ለመስራት እና ወደ ተግባር ለመግባት የሚያስችል ውይይት መሆኑ ተገልጿል።
ውይይቱ አምራቹ እና በገበያው ሰንሰለት ያለው ማህበረሰብ በትክከል እንዲጠቀም እንዲሁም በመሃል ያሉ እና ማነቆ የሆኑ ተዋንያንን ስርዓት ማስያዝ ከሰንሰለቱ ማስወጣት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ያኮረ ነው፡፡
የወርቅ ምርት አምራቹ ፈቃድ በአዲስ መልክ ማዘጋጀት እና ቀጥታ ወደ ብሄራዊ ባንክ የሚያስገባበት ስርዓት መዘርጋቱ የተገለፀ ሲሆን÷ አሰራሩም በየወሩ እየተገመገመ መሆኑን ኢንጂነር ታከለ ገልጸዋል፡፡
በክልሎች ምርቱ የሚወጣባቸው አካባቢዎች መለየታቸውን እና አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ ከፌደራል ፖሊስ ጋር ወደ ተግባር ለመግባት ተወስኗል ተብሏል።
ምርቱን በብዛት እና በጥራት ለማምረት የጸጥታ ሁኔታው አስተማማኝ መሆን አለበት ያሉት ኮሚሽነር ደመላሽ ይህ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
በፍሬሕይወት ሰፊው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version