አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትላንት ድል ባስመዘገባችሁበት የውቅን ተራራ ስር አዲስ አመትን ማክበራችን ልዩ ትርጉም ያለው ነው ሲሉ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሀኑ ጁላ ገለፁ።
ኢትዮጵያን ለማዳን ነው የምንዋጋው ያሉት ኢታማዦር ሹሙ አሸባሪ ቡድኑን አከርካሪውን በመምታት ዳግም እንዳይነሳ ለማድረግ ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል።
አሁን ተመትቶ የተዳከመው አሸባሪው ህወሀት ከ30ሺ በላይ ሚሊሺያ አዋጡ እያለ የትግራይ ህዝብን እያሰቃየ መሆኑን ተናግረዋል።
አሸባሪ ቡድኑ በሽንፋ፣ በአልመሀል በዳር፣ በመሀል ደግሞ ፅንፈኛውን ቅማንት ተጠቅሞ የጥፋት ተልዕኮውን ለመፈፀም የሞከረውን አሸባሪ ቡድን በደመሰሳችሁበት ማግስት የሚከበረው በአል የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን የድል ቀን ጭምር ነው ብለዋል።
ጄነራሉ ይህን አኩሪ ጀግንነት ለፈፀመው የምእራብ እዝ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
አሸባሪ ቡድኑ ራሱ የገነባውን ሰራዊት ከጀርባ የወጋ፣ ከአፋርና ከአማራ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ የተጣላ አብሮ መኖር የማይችል እኩይ ቡድን በመሆን ይህን ጠላት ለማጥፋትና የሀገር ህልውና ለማረጋገጥ ማንኛውንም መስዋዕትነት መክፈልም የሚያኮራ ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

