Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከተማ አስተዳደሩ የነዋሪችን የለውጥና የልማት ፍላጎቶች በመለየት ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል -ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪችን የለውጥና የልማት ፍላጎቶች በመለየት ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል፡፡
አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የምስረታ ስነ-ስርአት እየተካሄደ ነው፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው በሙሉ ድምጽ ተመርጠው ቃለመሃላ ፈፅመዋል።
ወይዘሮ አዳነች የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ በመሆን ለተሰጣቸው እድል አመስግነው ፥በከንቲባነት ሃላፊነቴ ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳልል የምችለውን ሁሉ ሰርቼ የጣላችሁብኝን አደራ በታማኝነት ለመወጣት ቃል እገባለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
6ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሁለንተናዊ የህዝብ ተሳትፎ ፣ፍላጎትና ቁርጠኝነት የታየበት የአዲስ ምዕራፍ መክፈቻ ነው ብለዋል፡፡
ምርጫው ከአንድ ምርጫ ሂደት በላይ የማንነትና የህልውና ነው በሚል የፀና እምነትና ቁርጠኝነታቸውን ባሳዩ መላ ኢትዮጵያውያን፤ ጠላቶቻችንን በአደባባይ ሽንፈት የተከናነቡበትና ፤ ከእውነትና ከኢትዮጵያ ጎን ለቆሙ አጋሮቻችንን ደግሞ ኩራት መሆን የቻልንበት፤ በዚህም ሀገር ወደ አዲስ ቀጣይ ምዕራፍ ያሸጋገርንበት ምርጫ አካሂደናል ብለዋል፡፡
ለዚህ አዲስ ምዕራፍ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት በሙሉም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ ባደረጉት ንግግርም “መሪዎቼን እመርጣለሁ” ብሎ ዝናብ እና ጸሃይ ሳይበግረው እስከ ውድቅት ሌሊት ለሰአታት ተሰልፎ የስልጣን ውክልናውን የሰጠንን የአዲስ አበባ ህዝብ እጅግ አመሰግናለሁ ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪችን የለውጥና የልማት ፍላጎቶች በመለየት ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል፡፡
ከወግ አጥባቂና ፅንፈኝነት ዝንባሌዎችና አፍርሶ ከሚገነባ አስተሳሰብ ተላቅንና መካከለኛውን መንገድ ይዘን ሁሉንም ኢትዮጵያውያን የሚያሰባስብ አካታች ፖለቲካዊ ጉዞ ተግባራዊ እናደርጋለንም ነው ያሉት፡፡
እንዲሁም አዲስ አበባን በአዲስ የዴሞክራሲ ባህል በአዲስ ምዕራፍ እንድትጓዝ ታሪካዊ ሃላፊነታችንን እንደምንወጣ አረጋግጣለሁ ሲሉም ገልፀዋል፡፡
የመኖሪያ ቤት፣የውሃና የመብራት አገልግሎት በጥራት ተደራሽ እንዲሆን ፣ለስራ እድል ፈጠራ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ፤ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ፣ የህግ የበላይነትን ለማስከበር በትኩረት እንደሚሰራ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም የትምህርት ስርዓትን ተደራሽ ለማድረግ ፤ሴቶች እና ህፃናትን መሰረት ያደረጉ የጤና ስርዓትን ለመዘርጋት ከተማ አስተዳደሩ ይሰራል ብለዋል፡፡
“መሪዎቼን እመርጣለሁ” ብሎ ዝናብ እና ጸሃይ ሳይበግረው እስከ ውድቅት ሌሊት ለሰአታት ተሰልፎ የስልጣን ውክልናውን የሰጠንን የአዲስ አበባ ህዝብ እጅግ አመሰግናለሁ ብለዋል።
በዚህም በከንቲባነት ሃላፊነቴ ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳልል የምችለውን ሁሉ ሰርቼ የጣላችሁብኝን አደራ በታማኝነት ለመወጣት ቃል እገባለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
በፌቨን ቢሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version