አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬ ባካሄደው የመጀመሪያ ጉባኤው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቧቸውን የካቢኔ አባላት አፅድቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው በምክር ቤቱ የተመረጡት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለካቢኔ አባልነት ባቀረቧቸው ዕጩዎች ላይ አስተያየትና ድምፅ ከሰጠ በኋላ ነው ሹመቱን ያፀደቀው።
በዚህም መሰረት፦
1 አቶ ጃንጥራር አባይ – ምክትል ከንቲባና የስራ፤ኢንተርፕራይዝ እና
ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ
2. አቶ መለስ ዓለሙ – የምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ
3. – አቶ ጥራቱ በየነ – በምክትል ከንቲባ ማእረግ የከተማ ስራ አስኪያጅ
4. ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን –በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ
ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ
5. ወይዘሮ ነጂባ አክመል – የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ
6. ወይዘሮ ያስሚን ወሃቢ –በምክትል ከንቲባ ማእረግ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ
7. አቶ አለማየሁ እጅጉ – የመንግስት ረዳት ተጠሪ
8. አቶ ተተካ በቀለ- የመንግስት ረዳት ተጠሪ
9. ዶክተር ቀንኣ ያደታ- የሰላም ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ
10. ዶክተር ሂሩት ካሳው- የባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ
11. ወይዘሮ ጽዋዬ ሙሉነህ – የፍትህ ቢሮ ሃላፊ
12. አቶ ጀማል ማንዬ -የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ
13. አቶ ዳዊት የሺጥላ – የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ
14. ኢንጂነር አያልነሽ ሃብተማርያም -የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
ሃላፊ
15. ዶክተር ሙሉቀን ሃብቱ – የቴክኒክ ሙያ፣ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ
ልማት ቢሮ ሃላፊ
16. አቶ አደም ኑር -የንግድ ቢሮ ሃላፊ
17. ዶክተር ዩሃንስ ጫላ- የጤና ቢሮ ሃላፊ
18. ዶክተር ዘላለም ሙላቱ – የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
29. ዶክተር ሃና የሺንጉስ – የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ
20. አቶ ግርማ ሰይፉ – የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
21. አቶ የሱፍ ኢብራሂም -የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን
ሃላፊ
22. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ – የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ
23. አቶ አብርሃም ታደሰ – የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ
24. አቶ ዮናስ ዘውዴ – የኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ
25. ወይዘሮ ጽጌሬዳ ወርቁ- የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ሃላፊ
26. ዶክተር ዳዲ ወዳጆ – የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው
ተሹመዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!