አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህጋዊ እውቅና ሳያገኙ ድሮኖችን የሚጠቀሙና ሲያበሩ የሚገኙ አካላት በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አሰታወቀ፡፡
አገልግሎቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን በሀገሪቱ በሚካሄዱ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ህዝባዊ ሁነቶች ላይ ቀረፃ የሚያካሂዱና ሲያበሩ የሚገኙ አካላት ከህገውጥ ከህገ ወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሀገሪቱን ደህንነትና ብሔራዊ ጥቅም የመጠበቅ ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም መሆኑ አስታውሶ ÷ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ለቀረፃ ሲጠቀም እና ሲያበር የተገኘ ማንኛውም አካል ወይም ግለሰብ በህግ እንደሚጠየቅ አስጠንቅቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!