አዲስ አበባ ፣መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በፅህፈት ቤታቸው አማካኝነት አሸባሪው የህወሓት ቡድን በፈጸመው ወረራ ምክንያት ከቄያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 650ሺ ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረጉ።
መንግስት ከሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ በተጨማሪም በግላቸው ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
በዛሬው ዕለትም የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ፣ አልባሳት፣ አልሚ ምግቦች፣ ሳኒታይዘርና አፍ መሸፈኛና የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ መንግስት ዜጎችን መታደግና መልሶ ማቋቋም ዋነኛ ሥራው እንደሚሆን ጠቁመው፤ ዜጎች ወደ ሠላማዊ ኑሯቸው እንደሚመለሱ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት አስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ተረፈ ፥ድጋፉ ከቀይ መስቀል ጋር በመተባበር የተገኘ መሆኑን ጠቅሰው 650ሺ ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ ነው ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል ።
ፕሬዝዳንቷ ባለፈው ሳምንት አሸባሪው ህወሓት በቀሰቀሰው ጦርነት ሳቢያ ከሰሜን ወሎና ደቡብ ወሎ ዞን ያፈናቀላቸውን ዜጎች ደሴና ኮምቦልቻ ከተማ በመገኘት አበረታትተዋል።
በህግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት ጉዳት ደርሶባቸው በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና በመረዳት ላይ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የክልል ልዪ ኃይሎችና የሚልሻ አባላትን “አይዟችሁ ከጎናችሁ ነን” ማለታቸው ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!