Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያን ለመቀየር ሰማይ መቧጠጥ አይጠበቅብንም – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ሀብቶች አቧራ ለብሰውና ቋጥኝ ተጭኗቸው የሚገኙ በመሆናቸው አገራችንንን ለመቀየር ሰማይ መቧጠጥ አይጠበቅብንም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስገነዘቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አዲስ በተዋቀረው ካቢኔ ለከፍተኛ አመራሮች ስልጠና በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ዛሬ ሲጀምር በሰጡት የሥራ መመሪያ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ አቧራ ለብሰውና ቋጥኝ ተጭኗቸው የሚገኙ በርካታ ሀብቶችን አውጥቶ ለጥቅም ማብቃት የአመራሩ ተልዕኮ ነው ብለዋል።

የዓላማ ጽናት ስንላበስ ጫና ፣ ግፊት እና መከራ የኢትዮጵያን ብልጽግና በር የሚከፍቱ እንጂ የሚያዳፍኑ አይደለም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያገለግሉትንና የሚገለገሉበትን ጠንቅቆ እንደሚያውቅ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ በስልጣን ላይ ስንቀመጥ ሰው መሆናችንን ሳንረሳ ፥ አሻራ ለማስቀመጥ ተግተን ከሰራን ውጤት ከደጃችን ነው ብለዋል።

የስልጠናው ዓላማም ማሳወቅ፣ ማነሳሳት፣ ለቡድን ሥራ ማዘጋጀትና ውጤታማ ማድረግ እንደሆነ አስታውቀዋል።

 

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version