አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተወሰኑ ዓለም አቀፍ የሰብዊ እርዳታ ድርጅቶች በአንድ አካባቢ ብቻ ድጋፍ እናድርግ የሚሉት ሃሳብ ተቀባይነት እንደሌለው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ከበደ ዴሲሳ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም አንዳንድ የምዕራባውያን የእርዳታ ድርጅቶች መንግስት የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ እንቅፋት ሆኗል የሚሉት ሃሳብ ተቀባይነት እንደሌለው ተናግረዋለ፡፡
የተወሰኑ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድርጅቶች ከሰብዓዊ ስራዎች ይልቅ ፖለቲካዊ ትርፍ ላይ አተኩረዋል ነው ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው፡፡
ተቋማቱ የሽብር ቡድኑ ህወሓት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በሚገኙ ዜጎች ላይ የሚያደርሳቸውን ሰብዓዊ ጥሰቶች ለማንሳት እንደማይደፍሩም አንስተዋል፡፡
ይህም ወራሪው ቡድን እየፈጸመ ያለውን ወንጀል ለመደበቅ ብሎም የእራሳቸውን ድብቅ ፍላጎት ለማሳካት የሚደርጉት ሴራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በሌላ በኩል ሰብኣዊ እርዳታ ጭነው ትግራይ ከገቡ 1 ሺሕ 114 ተሽከርካሪዎች ውስጥ 872ቱን አሸባሪው ሕወሓት ለጦርነቱ ታጣቂዎቹን ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ እየተጠቀመባቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በአማራና በአፋር ክልሎች አሸባሪ ቡድኑ ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች ለችግር የተዳረጉ ዜጎች ከአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ እንደሚበልጥ የተናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው÷የተወሰኑ ተቋማት በእነዚህ አካባቢዎች እርዳታ ለማሰራጨት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
መንግስት በሁለም አካባቢዎች የሰብዓዊ እርዳታ እንዲዳረስ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን በማንሳትም÷ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ሁሉንም ዜጎች በእኩል እንዲያዩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!