አዲስ አበባ ፣ ህዳር 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪ ቡድኑ ህወሓት የትምህርት ዘርፉን ኢላማ አድርጎ እየሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ቡድኑ የትምህርት ዘርፉን ኢላማ አድርጎ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፥ የተወሰኑ ትምህርት ቤቶች የመዝጋት አዝማሚያ ማሳየታቸውን ገልጸዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም 7 ማህበረሰብ አቀፍ እና 19 ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ያለበቂ ምክንያት የመማር ማስተማር ሂደት ማቆማቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር ለ3 ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ይፋዊ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መፃፉንም ነው የገለፁት።
በመግለጫቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ዜጎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት የጦር መሳሪያዎች ማስመዝገባቸውን ጠቅሰው፥ ከዚህ ጋር በተያያዘ ህገወጥ መሳሪያዎች መያዛቸውንም አስረድተዋል።
በቅርቡ የኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች ምዝገባም ተጀምሯል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ፥ ወታደራዊ የቅኝት መሳሪያዎች፣ ኮምፓስ፣ የጦርሜዳ መነፅሮች፣ የመገናኛ ሬዲዮ፣ ድሮን፣ የሳተላይት ኔትወርክ በአስራ አምስት ቀናት ዜጎች ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ዜጎች ወቅታዊውን ሁኔታ ከግምት በማስገባት በ933 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል።
በአፈወርቅ እያዩ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!