አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካና የምዕራባውን ተቋማት ከሚያወጡት መግለጫ በተቃራኒ አዲስ አበባ እንደተለመደው ሰላም ናት ፣ ይልቁንም የቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ ከአሜሪካ በመጡ አውሮፕላኖች ተሞልቷል ሲል የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኙ ላውረንስ ፍሪማን ገለጸ።
ከ30 ዓመታት በላይ በአፍሪካ የፖሊሲና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ምርምር በማድረግ የሚታወቀው ላውረንስ ፍሪማን በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ መግባቱን ገልጾ ፣ አዲስ አበባ የአሜሪካና የምዕራባውን ተቋማት ከሚያወጡት መግለጫ በተቃራኒው በተለመደ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ ላይ ትገኛለች ብሏል።
በከተማዋ የሚገኙ የንግድ ተቋማት፣ ሆቴሎች፣ ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በሙሉ አቅም አገልግሎት እየሰጡ ነው ሲልም አመላክቷል።
ይልቁንም የቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንግድ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከአሜሪካ በመጡ አውሮፕላኖች መሞላቱን ነው የገለጸው።
“ውሸትና ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ይቁም እዚህ አፍጋኒስታን የለችም የአገዛዝ ለውጥ ለማድረግ የሚካሄደው እንቅስቃሴም ይቁም” ሲል ማስታወቁንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!