አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት አራቱ የህመም ምልክቶችን ማሳየት ማቆማቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ።
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ 6 ታካሚዎች ናቸው።
ከእነዚህ ውስጥ አራቱ የህመም ምልክቶችን ማሳየት ያቆሙና በደህና ሁኔታ ላይ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።
ሁለቱ ታካሚዎች በማገገም ላይ በመሆናቸው የቅርብ ህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

