Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠ/ ሚ ዐቢይ ከጀኔራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን እና ከጀኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ጦር ዋና አዛዥ ጀኔራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን እና ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች ዋና አዛዥ ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ሁለቱ መሪዎች ልዩነቶቻቸውን በመግባባት እንዲፈቱ እና ለሀገራቸው መረጋጋትን ማምጣት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ታላቁ የሱዳን ሕዝብ ሰላም ያስፈልገዋል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

Exit mobile version