አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም በዩጋንዳ በፍልሰተኞች ጉዳይ ላይ በተዘጋጀው የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡
ጉባኤውን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ተቋም (ኢ ኤ ሲ) በጋራ ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ጉባኤው በፍልሰት እና መፍትሄዎቹ ላይ ያተኮረ መሆኑን በዩጋንዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
አቶ ብናልፍ ከጉባኤው በፊት ከተለያዩ የ ኢጋድ እና ኢ ኤ ሲ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር መምከራቸው ተጠቁሟል፡፡