Fana: At a Speed of Life!

አቶ ብናልፍ በዩጋንዳ በፍልሰተኞች ጉዳይ በተዘጋጀው የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም በዩጋንዳ በፍልሰተኞች ጉዳይ ላይ በተዘጋጀው የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

ጉባኤውን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ተቋም (ኢ ኤ ሲ) በጋራ ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጉባኤው በፍልሰት እና መፍትሄዎቹ ላይ ያተኮረ መሆኑን በዩጋንዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ብናልፍ ከጉባኤው በፊት ከተለያዩ የ ኢጋድ እና ኢ ኤ ሲ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር መምከራቸው ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.