Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በተዘጋጀው የ’ቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም’ የአቀባበል እራት ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6 2016 (ኤፍ ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በፕሬዚዳንት ጂንፒንግ በተዘጋጀው ቤልት ኤንድ ሮድ ፎረምየአቀባበል እራት ላይ ተገኝተዋል።

የቻይናው ፕሬዚዳንት ጂንፒንግ በመርሐ ግብሩ ላይ አቀባበል እንዳደረጉላቸውም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) እና የቻይናው ፕሬዚዳንት ጂንፒንግ ከየልዑካን ቡድናቸው ጋር በቻይና ታላቁ የሕዝብ አዳራሽ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (/) የቻይና ኢንቨስትመንት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እመርታ የሚኖረውን አስተዋፅዖ አንስተዋል፡፡

 

በተለይም በአምስቱ ቁልፍ ምሰሶዎች ማለትም÷ በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ አይሲቲ፣ ማእድን ልማት እና ቱሪዝም ላይ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እንዲኖር የማበረታቻ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

 

 

 

 

Exit mobile version