አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ከኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸው ሁለቱ ወገኖች በቀጠናዊና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ማሳደግ በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) በኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ተገኝተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከውን ልዩ መልክት ለፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ማድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡