አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ መጀመሪያ ላይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አኪንዉሚ አዴሲና ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በባንኩ መካከል ያለው ትብብርና ባንኩ የኢትዮጵያን ልማት ለመደገፍ በሚያደርገው ጥረት ዙሪያ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

